በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራዊው ቢስኪሌተኛ ቢኒያም ግርማይ ዐይኑ ላይ በደረሰበት ጉዳት ከውድድር ወጣ


ኤርትራዊው ቢስኪሌተኛ ቢኒያም ግርማይ
ኤርትራዊው ቢስኪሌተኛ ቢኒያም ግርማይ

ጂሮ ዲ ኢታሊያ በተባለው ዓለም አቀፍ የቢስኪሌት ውድድር የመጀመሪያ ዙር ያሸነፈ የመጀመሪያ አፍሪካዊ በመሆን ታሪክ የሰራው ኤርትራዊው ቢኒያም ግርማይ ዐይኑ ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ውድድሩን ለማቋረጥ እንደተገደደ ተገለጸ።

የሃያ ሁለት ዓመቱ ቢኒያም ትናንት ማክሰኞ በአስረኛው ምድብ ውድድር በማሸነፍ የመጀመሪያ አፍሪካዊ ሆኖ ያስመዘገበውን ታሪካዊ ድል ለማክበር ሻምፓኝ ሲከፍት ቡሹ ተፈናጥሮ ግራ ዐይኑን ጎድቶታል።

የቢስኪሌተኛው ቡድን ዶክተር ሲናገሩ፣

"ግራ ዐይኑ ተጎድቶ በመድማቱ በውድድሩ እንዳይሳተፍ ወስነናል፣ እናም ቢኒያም ያገኘውን ከፍተኛ ድል አስመዝግቦ ከውድድሩ ወጥቷል" ብለዋል።

ቢኒያም የሻምፓኙን ጠርሙስ ወለሉ ላይ አስቀምጦ አጎንብሶ ቡሹ የታሰረበትን ሽቦ ሲያላቅቀው ተፈናጥሮ ከቅርብ ርቀት መትቶታል። በደህና ሁኒታ ላይ ነው ያሉት ሃኪሙ ከውድድሩ እንዲወጣ የተወሰነው ጉዳቱ እንዳይባባስ በሚል ከባድ እንቅስቃሴ ከማድረግ እንዲቆጠብ ሃኪሞች አጥብቀው በመምከራቸው መሆኑን ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG