በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሪክ ያስመዘገበው ኤርትራዊው ቢስኪሌተኛ ቢኒያም ግርማይ ዐይኑ ላይ በደረሰበት ጉዳት ከውድድር ወጣ


ኤርትራዊው ቢስኪሌተኛ ቢኒያም ግርማይ
ኤርትራዊው ቢስኪሌተኛ ቢኒያም ግርማይ

ጂሮ ዲ ኢታሊያ በተባለው ዓለም አቀፍ የቢስኪሌት ውድድር የመጀመሪያ ዙር ያሸነፈ የመጀመሪያ አፍሪካዊ በመሆን ታሪክ የሰራው ኤርትራዊው ቢኒያም ግርማይ ዐይኑ ላይ በደረሰበት አደጋ ምክንያት ውድድሩን ለማቋረጥ እንደተገደደ ተገለጸ።

የሃያ ሁለት ዓመቱ ቢኒያም ትናንት በአስረኛው ምድብ ውድድር በማሸነፍ የመጀመሪያ አፍሪካዊ ሆኖ ያስመዘገበውን ታሪካዊ ድል ለማክበር ሻምፓኝ ሲከፍት ቡሹ ተፈናጥሮ ግራ ዐይኑን ጎድቶታል።

የቢስኪሌተኛው ቡድን የኢንተርማርሼ ዶክተር ሲናገሩ "ግራ ዐይኑ ላይ በደረስው ጉዳት በመድማቱ በውድድሩ እንዳይሳተፍ ወስነናል፣ እናም ቢኒያም ከፍተኛ ድል አስመዝግቦ ከውድድሩ ወጥቷል” ብለዋል።

ቢኒያም የሳምፓኙን ጠርሙስ ወለሉ ላይ አስቀምጦ አጎንብሶ ቡሹ የታሰረበትን ሽቦ ሲያላቅቀው ተፈናጥሮ ከቅርብ ርቀት መትቶታል። በደህና ሁኔታ ላይ ነው ያሉት ሃኪሙ ከውድድሩ እንዲወጣ የተወሰነው ጉዳቱ እንዳይባባስ ከባድ እንቅስቃሴ እንዲቅጠብ ሃኪሞች አጥብቀው በመምክራቸው መሆኑን ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG