በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጆርጂያው የምርጫ ውጤት የኢትዮጵውያንና ኤርትራውያን ድርሻ ምን ነበር?


ወ/ሮ ቤተለሄም ፍለሚንግ፣ ወ/ት ሀና ጆይ ገሥላሴ፣ እና ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወዬሣ ከአትላንታ ጆርጅያ
ወ/ሮ ቤተለሄም ፍለሚንግ፣ ወ/ት ሀና ጆይ ገሥላሴ፣ እና ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወዬሣ ከአትላንታ ጆርጅያ

በቅርቡ በጆርጅያ ክፍለ ግዛት የተደረገው የምክር ቤት እንደራሴዎች ምርጫ የመላው ዩናትድ ስቴትስን ትኩረ ስቦ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዚህም ምርጫ የዴሞክራቲክ ፓርቲ እጩዎች የሆኑት ራፋኤል ዎርኖክ እና ጆን ኦሰፍ የተባሉት አሸንፈዋል፡፡

ይህም ውጤት በሪፐብክሊካን ፓርቲ ቁጥጥር ስር የነበረው ምክርቤት ወደ ዴሞክራቶቹ ቁጥጥር እንዲዛወር አድርጓል፡፡ ይህ ለፕሬዛዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ፕሮግራምና ፖሊስዎች ቀና መንገድ ይከፍታል ተብሎ ተገምቷል፡፡

የጆርጅያ ክፍለ ግዛት በምክር ቤት አባላት ብቻ ሳይሆን በፕሬዚዳንታዊው ምርጫም ፕሬዚዳንቱን ለድል ካበቁት ክፍለግዛቶች አንዷ መሆኑም ይታወሳል፡፡

በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች በተለይም በቅርቡ በተደረገው ወሳኙ የሴነት ወይም የምክር ቤት አባላት ምርጫ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በክፍለ ግዛቱ የመምረጥ መብቱ አላቸው ከተባሉት ወደ 18ሺ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል፣ ምን ያህሉ ተመዝግበው ምን ያህሉ ለምርጫው እንደተሳተፉ መረጃ ባይኖርም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሳይመርጡ እንዳልቀረም ተገምቷል፡፡

በአትላንታ ከተማ ዙሪያ ብቻ፣ ለምርጫ ቅሰቅሳው በበጎ ፈቃደኝነት የተሳተፉት እንደሚሉት፣ “ወደ 12ሺ የሚሆኑ ትውልደ ኢትዮጵውያንና ኤርትራውያን ወጥተው እንዲመርጡ በቀጥታና በግል ቅሰቀሳ ያደረጉላቸው መሆኑን” ይናገራሉ፡፡

በጎ ፈቃደኞች መካከል ትውልደ ኢትዮጵዊቷ ወሮ ቤተልሄም ተመስገን ፊለሚንግና ትውልደ ኤርትራዊቷ ወ/ት ሀና ገብረ ሥላሴን እንዲሁም ሁኔታውን ተከታትሎ ሲዘግብ የነበረውን ከአትላንታ የአድማስ ሬዲዮ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወዬሣን አነጋግረናል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በጆርጂያው የምርጫ ውጤት የኢትዮጵውያንና ኤርትራውያን ድርሻ ምን ነበር?
please wait

No media source currently available

0:00 0:40:04 0:00


XS
SM
MD
LG