2013 ዓ.ም በማይካድራ ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 600 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። ኮሚሽኑ ዛሬ ይፋ ባደረገው የፈጣን ምርመራ ግኝት፤ ከጥቃቱ በኋላ ወደ ስፍራው የምርመራ ቡድን በመላክ ዘግናኝ የሆነ የሰባዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን ማረጋገጡን ገልጿል።
ጥቃቱም የተፈፀመው በትግራይ ሚሊሺያ አስተባባሪነት በሚታገዙና በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅር እና ‘ሳምሪ’ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን መሆኑንም ይፋ አድርጓል።
በሌላ በኩል አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ “ህወሓት” በሚያካሂዱት ጦርነት፤ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ሰላማዊ ዜጎች ደህንነት እንዲጠብቁ አሳሰበ።
በተጨማሪም መንግሥት የሰብዓዊ ረድኤት አቅራቢዎች ወደ ሥፍራው ገብተው ድጋፍእንዲሰጡ ሁኔታውን እንዲያመቻች ጥሪ አቀረቡ።
ወደ ማይካድራ፣ አብርሀጅራ፣ በሳንጃ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ እና በጐንደር በመዟዟር ጥናት ካሄዱት የኢሰመኮ አጥኒዎች መካከል አንዷ የሆነችውን ሃይማኖት አሸናፊን እና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች አጥኚ ፍሰሐ ተክሌን ያነጋገረችው ጽዮን ግርማ ዝርዝርሩን ይዛለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡