አዳማ —
ኢትዮጵያ ለአትክልትና ፍራፍሬ የሚሆን በቂ የእርሻ መሬትን ተስማሚ አየር ቢኖራትም የፍራፍሬ ምርቶችንና ተዋፅዖዎችን ከውጭ ታገባለች።
የፓፓያና አቮኬዶ ውጤት የሆኑ ምርቶችን በእሽግ ጭማቂ መልክ፣ እንዲሁም ሳሙናዎችንና ቅባቶችን ጭምር ትገዛለች።
ጥሬ ምርቶቿን ወደ ኢንዱስትሪ አስገብታ የመጠቀሟ ነገር ደካማ መሆኑ ግርምትን እንደሚፈጥርባቸው የሚናገሩ ብዙ አሉ።
ዘጋቢያችን ወደ ምሥራቅ ሸዋዪቱ ዱግዳ ወረዳ ሄዶ አቮካዶና ፓፓያ አምራች ገበሬዎችን አነጋግሯል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።