አዲስ አበባ —
አምራችና ሸማችን በቀጥታ ማገናኘቱ የሚነገርለት አዲስ አበባ ውስጥ የተጀመረውና የስድስት ሣምንታት ዕድሜ ያስቆጠረው “ኦሮ-ፍሬሽ ገበያ” የዋጋ ንረትን እንዲቀንስ በማድረግ እያገዘ መሆኑን አንዳንድ ሸማቾች እየተናገሩ ነው።
ኦሮ-ፍሬሽ የእርሻ ምርቶችን ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ ከአርሶ አደሮች ሰብስቦ ለዓለማቀፍ ገበያም ለማቅረብ አቅዶ የተጀመረ የገበያ ሰንሰለት መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ዶ/ር አደሬ አሰፋ አመልክተዋል።