በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሕግን ማስከበር መብቶችን በመጣስ መሆን የለበትም” - ኢሰመኮ


ፎቶ ፋይል፦ ደሴ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ ደሴ ከተማ

የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ "ሕግ የማስከበር ዘመቻ ሲል" በጠራው ዘመቻ ከ4 ሺሕ 500 በላይ ሰዎችን ሰሞኑን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም የፌዴራል መንግሥትና የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች “በተቀናጀ መንገድ የሕግ በላይነትን ማስከበር” በሚል ባለፉት ጥቂት ቀናት መውሰድ በጀመሩት እርምጃ ጋዜጠኞችና የማኅበረሰብ አንቂዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን ገልጿል።

"ሕግን ማስከበር መብቶችን በመጣስ መሆን የለበትም” - ኢሰመኮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:40 0:00

የተወሰኑት ታሳሪዎች በቤተሰቦቻቸው የተጎበኙና በተለያየ የጊዜ መጠን ወደ ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም በርካታ ታሳሪዎች ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ መታሰራቸውን፣ ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውን፣ በቤተሰብ አለመጎብኘታቸውን መመልከቱን ኢሰመኮ ጨምሮ ገልጿል።

“የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሂደት ሰብዓዊ መብቶችን በጣሰ መልኩ መሆን የለበትም” ሲሉ የኮሚሽኑ የሕግና ፖሊሲ ጉዳዮች ኃላፊ ወ/ሮ ታሪኳ ጌታቸው አሳስበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

"ሕግን ማስከበር መብቶችን በመጣስ መሆን የለበትም” - ኢሰመኮ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:59 0:00

XS
SM
MD
LG