በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና መሪዎች ውይይት


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የቻይና ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የቻይና ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የቻይና ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ትናንት ማክሰኞ ባካሄዱት የመጀመሪያቸው ንግግራቸው ግልጽነት በተመላበት መንገድ ተወያይተዋል ሲሉ የቢጂንግ እና የዋሽንግተን ባለሥልጣናት አድናቆት ሰጡ።

ውይይቱ ሁለቱ ሀገሮች በተለያዩ ትላልቅ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውጥረት ላይ ያለውን ግንኙነታቸውን ወደፊት የሚያራምድ ጎዳና ሊቀይስ እንደሚችልም አክለው ገልጸዋል።

ከአሁን ቀደም የሀገሮቻቸው ምክትል ፕሬዚዳንቶች በነበሩበት ጊዜ በአካል ተገናኝተው የሚያውቁት ሁለቱ መሪዎች በርዕሰ ብሄርነት የመጀመሪያቸው የሆነውን ውይይታቸውን ሰኞ ማታ በኢንተርኔት አማካይነት አካሂደዋል።

ሁለቱ መሪዎች አስቀድሞ ከተመደበው ግዜ አልፈው ከሦስት ሰዓት ተኩል በላይ ተነጋግረዋል። ሰብዓዊ መብቶችን፣ ኢኮኖሚያዊ ፉክክር እና የታይዋንን ጉዳይ ጨምሮ በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ መነጋገራቸው ተዘግቧል።

እኩለ ሌሊት ገደማ ላይ ውይይታቸው ከተጠናቀቀ በኋላ ዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዩናይትድ ስቴትስ ለጥቅሞቿ እና ለእሴቶችዋ መቆሟን እንደምትቀጥል አጠንክረው አስገንዝበዋል ብሏል።

አስከትሎም ከአጋሮቻችን ጋር ሆነን የሃያ አንደኛው ምዕተ ዓመት ጎዳና ህግጋት ግልጽ እና ፍትሃዊ የሆነ ዓለም አቀፍ ሥርዓት ለመመስረት ማስቻሉን ከሌሎች አጋሮቻን ጋር ሆነን መስራታችንን እንደምንቀጥል ፕሬዚዳንት ባይደን አሳስበዋል ብሏል።

የቻይና መንግሥት የዜና አገልግሎት ሺንዋ ትናንት ባወጣው መግለጫ ደግሞ የፕሬዚዳንት ባይደንን እና የፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ውይይት ግልጽ፣ ገንቢ እና መጠነ ሰፊ ነበር ካለ በኋላ ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ መንገዶች በቅርበት በመገናኘታቸውን በመቀጠል የሀገሮቻቸውን ግንኙነት ወደትክክለኛ አቅጣጫ ለመመለስ ሊሰሩ ተስማምተዋል ብሏል።

XS
SM
MD
LG