በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባይደን እና የፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ስብሰባ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና የቻይናው አቻቸው ዢ ጂንፒንግ ሰኞ በድረ ገጽ ውይይት አደረጉ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና የቻይናው አቻቸው ዢ ጂንፒንግ ሰኞ በድረ ገጽ ውይይት አደረጉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና የቻይናው አቻቸው ዢ ጂንፒንግ ትናንት “በሃገሮቻችን መካከል የሚደረጉ ውድድሮች በማወቅም ሆነ ባለመማወቅ ወደ ግጭት የማያስገቡን መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል” ሲሉ ትናንት ሰኞ በድረ ገጽ ላይ ባደረጉት ውይይት ተናገሩ፡፡

ታሪካዊ ነው በተባለው ውይይታቸው ሁለቱ መሪዎች ለሦስት ሰዓት ከግማሽ መወያየታቸው ከተጠበቀው በላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ዋይት ኃውስ ዛሬ ማለዳ ባወጣው መግለጫ “ፕሬዚዳንት ባይደን ከቻይናው መሪ ጋር፣ ስለሰብዓዊ መብቶች፣ ስለምጣኔ ሀብት ፉክክር፣ ስለ ታይዋን ፊት ለፊት ተገናኘተው አንድ በአንድ በግልጽና በቅንነት የመነጋገር እድል መኖሩን በደስታ እንደተቀበሉት አስታውቋል፡፡

ባይደን ቀደም ሲል ታዋይናን ከጥቃት ስለመከላከል የተናገሩትን በማለዘብ የዋይት ኃውስ ባወጣው መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ የታይዋንን ነጻ ሃገርነት እንደማትደግፍ ይልቁንም የአንድ ቻይና ፖሊስን እንደምትደግፍ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ዩናይትድ ስቴትስ ያለውን ሁኔታ በኃይል መቀልበስም ሆነ በታይዋን ባህር አካባቢ አለመረጋጋት እንዲፈጠር እንደማትፈልግ መግለጫው አመልክቷል፡፡ የቻይናውም መሪ ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ እንደተጠበቀው በሁለቱ ኃያላን ሃገሮች መካከል ብዙ ልዩነቶች መኖራቸውን ጠቅሰው ዩናይትድ ስቴትስና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለረጅም ጊዜ የቻይናን ሉዓላዊነት አስመልክቶ የሚያሳደሩትን ጫና ተከላክለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ “ሁላችንም የውስጥ ጉዳዮቻችንን በሚገባ እየፈታን፣ በዚያው መጠንም ዓለም አቀፍ ኃላፊነቶቻችንን በጋራ እየሠራን በመወጣት፣ በጎ ለሆነው የዓለም ሰላምና ብልጽግና ብንተጋ ይሻላል” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG