በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማድሊን ኦልብራይት የመጨረሻ ስንብት ተደረገላቸው


ፕሬዚዳንት ባይደን እና ሌሎች የዓለም መሪዎች፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዕውቅ የፖለቲካና የውጭ ፖሊሲ ሰዎች ትናንት ረቡዕ ለማድሊን ኦልብራይት የመጨረሻ ስንብት አደረጉላቸው።
ፕሬዚዳንት ባይደን እና ሌሎች የዓለም መሪዎች፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዕውቅ የፖለቲካና የውጭ ፖሊሲ ሰዎች ትናንት ረቡዕ ለማድሊን ኦልብራይት የመጨረሻ ስንብት አደረጉላቸው።

የዓለም መሪዎችና የዩናይትድ ስቴትስ ዕውቅ የፖለቲካና የውጭ ፖሊሲ ሰዎች ትናንት ረቡዕ በልጅነታቸው በጦርነት ከታመሰችው አውሮፓ በስደት መጥተው በዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያዋ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለመሆን የበቁትን የቀድሞዋን ዕውቅ ዲፕሎማት ማድሊን ኦልብራይትን የመጨረሻ ስንብት አድርገውላቸዋል፡፡

ስንብቱን የመሩት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና እንዲሁም ኦልብራይትን ከፍተኛ ዲፕሎማታቸው አድርገው በመሾም በወቅቱ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ካሉት ሴቶች ሁሉ የላቀውን ሥልጣን እንዲኖራቸው ያስቻሏቸው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ነበሩ፡፡

በዋሽንግተን ብሄራዊ ካቴድራል የኦልብራይትን ህይወትና አበርክቶ ለመዘከር በተካሄደው የስንብት ሥነ ሥርዓት ላይ ወደ 1ሺ400 የሚጠጉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን እንዲህ ብለው ተናገሩላቸው፣

“ነፃነት ሁሉንም መሰናክሎች ተቋቁሞ በእያንዳንዱ ጨቋኝ ፊት ይቆማል፡፡ ምክንያቱም ሁል ጊዜም ለነጻነት የሚፋለሙ ሰዎች አሉ፡፡ በ20ኛውና 21ኛው ክፍለ ዘመን ነጻነት ከማድሊን ኦልብራይት የተሻለ ሌላ ሻምፒዮን አልነበራትም፡፡”

ባላፈው ወር ውስጥ ህይወታቸው በካንሰር ያለፈው ኦልብራይት 84 ዓመታቸው ነበር፡፡

በእርሳቸው ሞት ከመላው ዓለም የዘነበው የሀዘን መልዕክት በርካታ ሲሆን፣ ለዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ይሰጡት የነበረው ድጋፍ ጎልቶ ከተነገረላቸው ውስጥ ነው፡፡

የኦልብራት ልጆች እናታቸው በልጅነታቸው ከትውልድ አገራቸው ከቺኮዝላቫኪያ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመጡበትን ጉዞ ፈጽሞ የማይረሱት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የማድሊን ልጅ አሊስ ፓተርሰን ኦልብራይትን እንዲህ ገልጸዋቸዋ፣

“እናታችን ዓለም አቀፍ በሆነ ጉዳይ ሁሉ ፍላጎት ትቀሰቅሳለች፣ በተለይ ለኔ፡፡ የችኮዝላቫኪያን ዳምፕሊንግ እየበላን፣ የቼክን ገና በዓል መዝሙሮች እዘመርን ነው ያደግነው፡፡ እኔና ኣን 12 ዓመታችን ኬት ደግሞ 6 ዓመቷ ነበር፡፡ ያን ጊዜ እሷና አባታችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአትላንቲክ ባሻገር ስዊዘርላንድ እና ፈረንሳይን እንድንጎበኝ ወሰዱን፡፡ እናቴ ፈረንሳይኛ መናገር ትወዳለች፡፡ አቀላጥፋ ከምትናገራቸው አምስት ቋንቋዎች አንዱ ሲሆን፣ እኛም እንድንማር ትገፋፋን ነበር፡፡ ለሷ ይህ ማለት ከኛ ውጭ ለሆነ አተያይ ሊሰጥ የሚገባው ክብርና ሊቀሰም የሚገባው ትምህርት እንደ ማለት ነው፡፡

ምንም እንኳ ውጭ አገር የተወለዱ በመሆናቸው ለፕሬዚዳንትነት መሰለፍ ባይችሉም ኦልብራይት ማለት በመላው ዓለም ሊባል በሚችል ደረጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደነቁ፣ የልዩነትን ግንብ ሰባሪ ሆነው፣ በፖለቲካ ባላንጣዎቻቸው ሳይቀር የተከበሩና የተወደዱ ሴት ነበሩ፡፡

የቀብር ሥነ ሥረዓታቸው ትናንት ረቡዕ ተፈጸመ፡፡

XS
SM
MD
LG