የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ትሬድ ማህበራዊ ሚዲያዎችን የሚያስተዳድረው ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሜታ፤ በማህበራዊ የትስስር ገጾቹ ላይ የሚተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቀነስ ከሶስተኛ ወገን ተቋማት ጋር በመተባበር ያካሂድ የነበረውን የመረጃ ማጣራት ስራ ማቋረጡ ሀሰተኛ መረጃዎች እና የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እንዲሰራጭ ያደርጋል ሲሉ ተቺዎች ተናግረውል። በአሁኑ ወቅት ውሳኔው በአሜሪካ ውስጥ ብቻ ተግባራዊ እንደሚደረግ ለአሜሪካ ድምፅ የገለጸው ፌስቡክ በበኩሉ፣ ከአሜሪካ ውጪ ወዳሉ ሀገራት ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ተቋሙ የሚኖሩበትን ግዴታዎች በጥንቃቄ እንደሚያጠና ገልጿል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)
መድረክ / ፎረም