እስራኤል በሊባኖስ የሚገኘውን የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን ለማጥፋት ከመስከረም ወር ጀምሮ እያካሄደች ባለችው የአየር ጥቃት ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን፣ ቤይሩት የሚገኝ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል። እኛ ለእኛ በስደት የተሰኘው በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች ባንቺ ይመር ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ እስራኤል ጥቃቱን አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅትም አዳዲስ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ቤይሩት መግባት መቀጠላቸውን አመልክተው፣ የኢትዮጵያ መንግስት አዲስ የተደረሰውን የተኩስ ማቆም ስምምነት ተጠቅሞ ዜጎቹን ከሊባኖስ እንዲያስወጣ እና ወደ ሊባኖስ የሚያቀኑ አዳዲስ ስደተኞችን እንዲያስቆም ጠይቀዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ፋይል ያገኛሉ)
መድረክ / ፎረም