የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ከሦስት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ በትግራይ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በግለሰቦች ላይ ማዕቀብ የጣለው ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ተፈጻሚነት የሚጸናበት የጊዜ ገደብ እንዲራዘም ወስነዋል።
ባይደን ከትላንት በስቲያ ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና ለእንደራሴዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በፃፉት ደብዳቤ መጀመሪያ ላይ ትዕዛዙ እንዲወጣ ያነሳሳው ጉዳይ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ለውጥ/መሻሻል አላሳየም በማለት አስፍረዋል።
ኢትዮጵያን በተመለከተ በፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ 14046 የታወጀው ብሄራዊ ድንገተኛ ጊዜ አዋጅ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ወስኛለሁ”
“በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እና ከዛ ጋር ተያየዞ ያለው ግንኙነት፤ የኢትዮጵያን ሰላም፣ ደኅንነት እና መረጋጋትን እና በሰፊው ደግሞ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን ሰላም፣ ፀጥታና መረጋጋት አደጋ ላይ በሚጥሉ ተግባራት የታየበት እና ባልተለመደ መልኩ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ፖሊሲ እና በብሔራዊ ደኅንነት ላይ ሥጋት መደቀኑን የቀጠለ ነው” ሲል ኋይት ሀውስ ያወጣው መግለጫ ዘርዝሯል።
ፕሬዝዳንቱ በደብዳቤያቸው አያይዘውም “ኢትዮጵያን በተመለከተ በፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ 14046 የታወጀው ብሄራዊ ድንገተኛ ጊዜ አዋጅ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ወስኛለሁ” ብለዋል።
ፕሬዝዳንታዊው ትዕዛዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በጎርጎርሳዊያኑ መስከረም 17/ 2021 በህወሓት ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል የነበረው ግጭት በተጋጋለበት ወቅት የወጣው ሲሆን፤ የአሁኑም የፕሬዘዳንቱ ውሳኔ ያ የቀደመ ትዕዛዝ የሚጸናበት የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ በመቃረቡ በድጋሚ የተወሰደ ነው።
መድረክ / ፎረም