በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወባ የከፋ ጉዳት እያስከተለ መኾኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ


በኢትዮጵያ የተከሠቱ የወባ፣ የኩፍኝ እና የኮሌራ ወረርሽኞች፥ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተሉ መኾናቸውን፣ የተባበሩት መንግሥታት እና የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቀዋል።

ዛሬ ረቡዕ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ ወረርሽኞቹን ለመከላከል አስፈላጊ ግብአቶች ተሟልተው በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነው፤ ሲሉ ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በምኅጻሩ ዩኤን-ኦቻ ደግሞ፣ ዛሬ ባወጣው ሪፖርቱ፣ በኢትዮጵያ እ.አ.አ ከጥር ወር እስከ ሰኔ ወር ባሉት ስድስት ወራት ብቻ፣ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸውን አመልክቷል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ፣ 182 ሰዎች በወባ መሞታቸውንም ጠቁሟል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:05 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG