የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ ሥርዓት እንዲመራ የወሰነው፣ አገሪቱ በዋጋ ንረት እና በሰላም ዕጦት ጫናዎች ውስጥ ባለችበት ወቅት ነው፤ ያሉ አስተያየት ሰጪዎች፣ “የኑሮ ውድነቱን ይበልጥ ሊያከብደው ይችላል፤” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
ስጋቱ፣ በተለይ በዝቅተኛ ደመወዝ በሚተዳደሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ማየሉ ተመልክቷል፡፡
መንግሥት፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አካል የኾነው የውጭ ምንዛሬ ተመንን በገበያ የመምራት ውሳኔው፣ በዝቅተኛ ገቢ በሚተዳደረው ማኅበረሰብ ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመቀነስ ተዘጋጅቻለኹ፤ ቢልም፣ በዓቅም እና በትግበራ ሊፈተን እንደሚችል ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡
በዐዲስ አበባ ከተማ ሾላ ገበያ አካባቢ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች፣ በትላንትናው ዕለት ተግባራዊ የኾነውን ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ውሳኔ ተከትሎ በተለያዩ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ ከወዲሁ የዋጋ ጭማሪዎች እየታዩ መኾናቸውን ተናግረዋል፡፡
ነዋሪዎቹ የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም