በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሩሲያ ሊያቀኑ ነው


የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንዲራ ሞዲ እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ብላድሚር ፑቲን በጎርጎርሳዊያኑ 2019
የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንዲራ ሞዲ እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ብላድሚር ፑቲን በጎርጎርሳዊያኑ 2019

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ነገ ሰኞ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ሞስኮ ይገባሉ። ጉብኝቱ ሞስኮ ከቻይና ጋር ግኙነቷን እያጠበቀች ባለችበት ወቅት የሚካሄድ ነው። የኒው ደልሂ የፖለቲካ ተንታኞች የመሪዎቹ ውይይት፤ የሩሲያ የረዥም ጊዜ አጋር የነበረችው ሕንድ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ግንኙነቷ እየጠበቀ መጥቷል የሚለውን አመለካከት ለመቅረፍ ይረዳል ብለዋል።

በኢንዶ ፓስፊክ ጥናቶች ላይ ያተኮረው የካሊንጋ ማዕከል መስራች የሆኑት ቺንታማኒ ማሃፓትራ “ምንም እንኳን ሩሲያ ከቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት ብታጠብቅም ሕንድ ከሞስኮ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እና ሩሲያ- ከቻይና ጋር የሚኖራት ግንኙነት ምንም ዓይነት ጫና እንደሌለው ማረጋገጥ ነው” ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

ጉባኤው ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ የመጀመሪያው ሲሆን፤ ኒው ዴሊህ ጦርነቱን ሳታወግዝ እና በሞስኮ ላይ ማዕቀብ የጣሉትን የምዕራባውያንም ባለመቀላቀል ገለልተኛ ሆና ቆይታለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG