በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔቶ በሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ግንኙነት ዙሪያ ይወያያል


የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያው ፕሬዘዳንት ብላድሚር ፑቲን ሰኔ 2016/ዓ.ም
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያው ፕሬዘዳንት ብላድሚር ፑቲን ሰኔ 2016/ዓ.ም

በዚህ ሳምንት የሚጀምረው የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ጦር ኔቶ ጉባዔ ከሚወያይባቸው ጉዳዮች መካከል፤ በሩሲያ እና በሰሜን ኮሪያ መካከል እየተጠናከረ የመጣውን ወታደራዊ ትብብር ተከትሎ፤ ከደቡብ ኮሪያ እና ከጃፓን ጋር የደህንነት ግንኙነት ማጠናከርን የተመለከተው ዋነኛው ነው።

ከመጭው ማክሰኞ ሐምሌ ሁለት እስከ ሐሙስ ሐምሌ አራት 2016 ዓ.ም ድረስ 32 የኔቶ አባል ሀገራት መሪዎች በዋሺንግተን ዲሲ ይሰባሰባሉ። ስብሰባቸው ከሁለት ዓመታት በፊት ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተክትሎ አባል ሀገራቱ ለዩክሬን አጋርነታቸውን ለማሳየት ስለሚያደርጉት ወታደራዊ ድጋፍ ላይ የሚያተኩር ይሆናል።

አልፎ አልፎ ኢንዶ ፓስፊክ በመባል የሚጠሩት አውስትራሊያ፣ ጃፓን፣ ኒው ዚላንድ እና ደቡብ ኮሪያ በኔቶ ጉባዔ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል። ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ በጉባዔው ትይዩ ውይይት ያደርጋሉ።

የሩሲያው ፕሬዘዳንት ባለፈው ወር ላይ ከፒዮንግያንግ ጋር የመከላከያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ፤ ሰሜን ኮሪያ በሩሲያ ይዞታ ስር በምትገኘው ዶኔስክ የጦር መሃንዲሶችን እንደምትልክ ጥርጣሬዎች አሉ። የፔንታገን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፓትሪክ ሬይደር በጎርጎርሳዊያኑ ሰኔ 25 በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ፤ ሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ኃይሎችን እንዳትልክ አስጠንቅቃለች ያሉ ሲሆን አያይዘውም “በዩክሬን ላይ ህገወጥ በሆነው ጦርነት የመድፍ እራት” ይሆናሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ከሁለት ቀን በኋላ በጎርጎሮሳዊያኑ ሰኔ 27 ሰሜን ኮሪያ “በፍትሃዊው ጦርነት ሁልጊዜ ከሩሲያ ሰራዊት ጋር እናብራለን” ስትል አስታውቃለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG