በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመርዓዊ ከተማ የተካሄደው ግድያ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ

የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች፣ በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋራ ያደረጉትን ውጊያ ተከትሎ፣ ጥር 20፣ 2016 ዓ.ም ባልታጠቁ ሰዎች ላይ ፈጽመውታል የተባለው ግድያ በአስቸኳይ በአፍሪካ እና ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች ተቋማት እንዲመረመር፣ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ የመብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

አምነስቲ አርብ ዕለት ባወጣው ሪፖርት፣ ጥር 21 በከተማው በሚከበረው ዓመታዊ የቅድስት ማሪያም በዓል ዋዜማ የኢትዮጵያ ወታደሮች የአካባቢውን ሰዎች ከየቤታቸው፣ ከየሱቆቻቸው እና ከመንገድ ላይ ከሰበሰቡ በኃላ በጥይት ተኩሰው መግድላቸውን ነዋሪዎች እንደገለፁ አመልክቷል።

የተቋሙ የምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ታይግሪ ቻጉታህ "በኢትዮጵያ ጅምላ ግድያ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተለመደ መጥቷል" ማለታቸውንም ጨምሮ ጠቅሷል።

በመርዓዊ ከተማ የተፈፀመውን ግድያ ለማጣራት አምነስቲ አራት የሟች ቤተሰቦችን እና አምስት የሟቾችን አስክሬን ከመንገድ በማንሳት የተባበሩ ሰዎችን ጨምሮ 13 ሰዎች ማነጋገሩን እና የቪዲዮ እና የሳተላይት ምስሎችንም ማጣራቱን አስታውቋል።

ነዋሪዎቹ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በተኩስ ድምፅ እና በከባድ የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ከእንቅልፋቸው መንቃታቸውን ለአምነስቲ የገለፁ ሲሆን ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር የተካሄደው ውጊያ ከተጠናቀቀ እና ታጣቂዎቹ ከተማውን ጥለው ከወጡ በኃላ የመንግስት ኃይሎች ቤት ለቤት በመዘዋወር በጅምላ መግደላቸውን ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ኮሚሽን እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተቋማት ግድያዎቹን ለማጣራት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ የጠየቀው አምነስቲ ኢንተርናሽናል "በአማራ ክልል እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰት እየቀጠለ በመሆኑ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ፍትህን ለማስፈን ቁርጠኝነት ባለመኖሩ" ሥራው የተቋረጠው እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስር በኢትዮጵያ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን እንዲመረምር ተቋቁሞ የነበረው ቡድን ዳግም ሥራውን እንዲቀጥል ጠይቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG