በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ 'አፈርማቲቭ አክሽን' መቀልበስ በተማሪዎች ላይ ምን ተፅእኖ አለው?


የአሜሪካ 'አፈርማቲቭ አክሽን' መቀልበስ በተማሪዎች ላይ ምን ተፅእኖ አለው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:08 0:00

የአሜሪካ 'አፈርማቲቭ አክሽን' መቀልበስ በተማሪዎች ላይ ምን ተፅእኖ አለው?

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ጥቁሮችን፣ ሴቶችን እና ሌሎች አናሳ የማህበረሰብ ክፍሎችን ጨምሮ፣ በአሜሪካ የሀብት ድልድል ተካፋይ ያልሆኑ ወይም አድልዎ ተደርጎባቸዋል ተብለው የሚታሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን ዘርን ያገናዘበ መመልመያ ፖሊሲ (አፈርማቲቭ አክሽን) ከዚህ በኃላ ተፈፃሚ እንዳይሆን ውሳኔ ካሳለፈ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩንቨርስቲዎች አዲስ ተማሪዎችን ወደ ተቋማቸው እየተቀበሉ ነው።

በርዕዮተ ዓለም መስመር የተከፋፈሉት የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድቤት ዳኞች ስድስት ለሶስት በሆነ ድምፅ፣ ላለፉት 45 አመታት በስራ ላይ የኖረውን ፖሊሲ መቀየራቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚኖረው የትምህርት ዕድል እና የዘር ስብጥር ላይ ምን አይነት ተፅእኖ ይኖረዋል ስንል፣ በሚኖሶታ የከተማ ምክር ቤት የፍትሃዊነት እና የእኩል ዕድል ቢሮ ረዳት ዳይሬክተር የሆኑትን የህግ ባለሙያ አቶ ዘካሪያስ ሀይሉ አነጋግረናቸዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG