በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በባልትሞር የፈረሰውን ድልድይ ለመተካት ቢያንስ 400 ሚሊዮን ዶላር ይፈጃል ተባለ


ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት በአንድ መርከብ ተገጭቶ የፈረሰው የፍራንሲስ ስካት ድልድይ ሜሪላንድ፣ ባልቲሞር እአአ መጋቢት 9/2024
ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት በአንድ መርከብ ተገጭቶ የፈረሰው የፍራንሲስ ስካት ድልድይ ሜሪላንድ፣ ባልቲሞር እአአ መጋቢት 9/2024

ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት በአንድ መርከብ ተገጭቶ የፈረሰውንና በባልትሞር ከተማ የሚገኘውን የፍራንሲስ ስካት ድልድይ ለመጠገን በትንሹ 400 ሚሊዮን ዶላርና ከአምስት እስከ ሰባት ዓመታትን እንድሚፈጅ የምሕንድስና ባለሞያዎች በመናገር ላይ ናቸው።

የፕሬዚደንት ባይደን አስተዳደር በበኩሉ ከሜሪላንድ ክፍለ ግዛት የተጠይቀውን 60 ሚሊዮን ዶላር የፌዴራል መንግሥት አስቸኳይ ርዳታ ለክፍለ ግዛቱ ልኳል።

የአሜሪካ ወታደራዊ መሃንዲሶች ቡድን ትልቅ የተባለውን ክሬን ወደ ስፍራው በማስጠጋት የድልድዩን ፍርስራሽ ለማንሳት በመዘጋጀት ላይ ናቸው።

የመርከቦች ዝውውር አሁንም እንደታገደ ሲሆን፣ ፍርስራሹን የማንሳት ሥራ ሲጠናቀቅ መልሶ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

በአደጋው ወቅቱ በሥራ ላይ የነበሩ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ፣ የአራቱ አስከሬን እስከ አሁን አልተገኘም። ፍርስራሹ የአስከሬን ፍለጋውን በማስተጓጎሎ ለጊዜው ተቋርጧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG