ፓርቲው በስም ከጠቀሳቸው ሟቾች መካከል የሁለቱ እህት እንደሆኑ የተናገሩ አንዲት ወይዘሮ፣ ወንድሞቼ ለክብረ በዓል በሔዱበት የአቦ ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በመከላከያ ሠራዊት አባላት በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል፤ ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡የአገሪቱ ወታደራዊ እና ሲቪል ባለሥልጣናት በቅርቡ በሰጧቸው አስተያየቶች፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊትም ኾነ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች በአጠቃላይ፣ ሲቪሎችንም ኾነ የሲቪል ተቋማትን ዒላማ አያደርጉም፤ ሲሉ መሰል ውንጀላዎችን ተከላክለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
በጊዳ አያና ወረዳ አሥር ሲቪሎች ላይ የበቀል ግድያ መፈጸሙ ተገለጸ
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ማርች 10, 2025
የአሜሪካ ታጋቾች ተደራዳሪ ከሐማስ ጋራ የነበራቸውን ንግግር “ጠቃሚ” ብለውታል
-
ማርች 08, 2025
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማርች 8ትን በሴቶች ብቻ በሚደረጉ በረራዎች እያከበረ ነው
-
ማርች 07, 2025
የክዋኔ ጥበብ እና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ
-
ማርች 07, 2025
ጥንቃቄ የሚሻው የወጣቶች የማኅበራዊ ሚድያ አጠቃቀም