በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሽግግር ፍትሕ ትግበራ በፊት ግጭቶች እንዲፈቱ የሲቪል ማኅበራት ጠየቁ


ከሽግግር ፍትሕ ትግበራ በፊት ግጭቶች እንዲፈቱ የሲቪል ማኅበራት ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:18 0:00

ከሽግግር ፍትሕ ትግበራ በፊት ግጭቶች እንዲፈቱ የሲቪል ማኅበራት ጠየቁ

በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሰላም ዕጦት፣ የሽግግር ፍትሕን ለመተግበር እንደማያስችል የገለጹ ስምንት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ በቅድሚያ ግጭቶች መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠየቁ። ድርጅቶቹ፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን አስመልክተው ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ መንግሥት ከግምት ማስገባት ይኖርበታል ያሏቸውን ልዩ ልዩ ምክረ ሐሳቦች አቅርበዋል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ “ከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፈጽሟል የተባለው የኤርትራ ሠራዊትም ተጠያቂ የሚሆንበት አሠራር ሊኖር ይገባል፤” ብለዋል፡፡

መግለጫውን ካወጡት ድርጅቶች አንዱ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዲሬክተር አቶ ያሬድ ኀይለ ማርያም ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ረቂቅ ከመጽደቁ በፊት ለውይይት መቅረብ እንዳለበት አመልክተዋል፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ዘገባ ያገኛሉ)

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG