በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሴቶች መብቶች የምትሟገተው ሚልድሬድ


ለሴቶች መብቶች የምትሟገተው ሚልድሬድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:27 0:00

ለሴቶች መብቶች የምትሟገተው ሚልድሬድ

ከ20 ዓመታት በፊት ጆን አለን ሙሐመድ የተባለ አልሞ ተኳሽ፣ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ላይ አነጣጥሮ በመተኮስ 10 ሰዎችን ሲገድል ሦስት ሰዎችን ክፉኛ አቁስሎ ነበር።

ለ23 ቀናት የቆየው ጥቃት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉና ነዋሪዎችም ከቤታቸው እንዳይወጡ አስገድዶ ነበር። ለ12 ዓመታት አብራው በትዳር የቆየችው ባለቤቱ ሚልድሬድ ሙሐመድ ግን፣ ከባሏ ስሜታዊ እና አእምሯዊ ጥቃት ጋራ ከዚያ በላይ አብሯት መኖሩን ትናገራለች። ባሏ ሊገድላት እንደሚፈልግ አውቃ ርዳታ ብትጠይቅም ጆሮ የሚሰጣት ግን አልነበረም።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ መሠረት፣ ከሦስት ሴቶች አንዷ ቢያንስ በሕይወት ዘመኗ አንድ ጊዜ እንደ ሚልድሬድ ሙሐመድ የቤት ውስጥ ጥቃት ይደርስባታል።

አሁን ለሴቶች መብት ከምትሟገተው ሚልድሬድ ጋራ ቆይታ ያደረገችው ስመኝሽ የቆየ፣ የቤት ውስጥ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ስለሚደርስባቸው ተጽእኖ እና ከጉዳቱ ማገገም የሚችሉበትን መንገድ በተመለከተ አነጋግራታለች። ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG