በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሸገር ከተማ የታሰሩ የሃይማኖት አባቶች የዐሥር ቀን ቀጠሮ ተጠየቀባቸው


በሸገር ከተማ የታሰሩ የሃይማኖት አባቶች የዐሥር ቀን ቀጠሮ ተጠየቀባቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:01 0:00

በደቡብ ወሎ ዞን ለጎ ሐይቅ አካባቢ በ“ገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክት ከመሬታቸው የተነሡ አርሶ አደሮች፣ ተገቢውን ካሳ አለማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡

ካሳው መንግሥት ባስቀመጠው ቀመር እንዳልተሰላ የጠቀሱት አርሶ አደሮቹ፣ ጠቅላላ ክፍያውም ከምርታቸው ያገኙ ከነበሩት ያነሰና ከኑሮ ውድነቱም ጋራ እንደማይመጣጠን ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል መሬት ቢሮ በበኩሉ፣ የካሳ ስሌቱ መመሪያውንና ደንቡን መሠረት አድርጎ እንደተሠራ ገልጾ፣ እስከ አሁን በጉዳዩ ላይ ለቢሮው የቀረበ ቅሬታ አለመኖሩን አስታውቋል፡፡

ጥያቄ ያላቸው አርሶ አደሮች፣ በወረዳ እና በዞን ደረጃ ለተቋቋመው ኮሚቴ ማቅረበ እንደሚችሉም አመልክቷል፡፡ በአንጻሩ አርሶ አደሮቹ፣ ቅሬታቸውን ለማቅረብ ተጽእኖ እንደተደረገባቸው ጠቁመዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከሐይቅ ከተማም ሆነ ከደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG