በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳላህ ቋንጃው ላይ ለደረሰበት ጉዳት ዛሬ ምርመራ ይደረግለታል - የቡድኑ ሐኪም


ግብጻዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሞሃመድ ሳላህ
ግብጻዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሞሃመድ ሳላህ

ግብጻዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሞሃመድ ሳላህ ትናንት አገሩ ከጋና ብሄራዊ ቡድን ጋር በነበረባት ግጥሚያ ወቅት በቋንጃው አካባቢ የደረሰበት ጉዳት እንደሚመረመር የብሄራዊ የቡድኑ ሐኪም አስታውቀዋል።

የሊቨርፑሉ አጥቂ ስላህ፣ ትናንት ግብጽ ከጋና ጋር ሁለት ለሁለት በተለያየችበት የቡድን ቢ ጨዋታ ወቅት ከመጀመሪያው ግማሽ መጠናቀቅ ቀደም ብሎ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት አቋርጦ ለመውጣት ተገዷል።

ሳላህ ቋንጃው አካባቢ ውጋት ስላጋጠመው ተቀይሮ ሊወጣ ችሏል”

“ሳላህ ቋንጃው አካባቢ ውጋት ስላጋጠመው ተቀይሮ ሊወጣ ችሏል” ሲሉ የቡድኑ ሐኪም ሞሃመድ አቡ ኤሌላ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

ግብጽ ከኬፕ ቨርድ ጋር ሰኞ ላለባት ግጥሚያ መጫወት ይችል እንደሁ ዛሬ የሕክምና ምርመራ ይደረጋል ብለዋል ዶክተሩ።

የ31 ዓመቱ ሳላህ ባረፈበት ሆቴል ካለ ችግር ሲራመድ እንዳየው የኤኤፍፒ ዘጋቢ በሪፖርቱ አመልክቷል።

ግብጽ ሰኞ ከኬፕ ቨርድ ጋር ያለባት ጨዋታ፣ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ ከሚያልፉ 16 ቡድኖች አንዱ ለመሆን ወሳኝ ይሆናል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG