በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች በሀገራዊ ምክክር ሒደቱ መሳተፍ እንዲችሉ ጠየቁ


በዐማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች በሀገራዊ ምክክር ሒደቱ መሳተፍ እንዲችሉ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:33 0:00

በዐማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮች በሀገራዊ ምክክር ሒደቱ መሳተፍ እንዲችሉ ጠየቁ

በኢትዮጵያ እየተስፋፉ ባሉ ግጭቶች ምክንያት፣ ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬ የተፈናቀሉ ዜጎች፣ በሀገራዊ ምክክር ሒደቱ እንዲሳተፉ ምቹ ኹኔታ እንዲፈጠርላቸው፣ ኮሚሽኑን ጠየቁ፡፡

በአሁኑ ወቅት በዐማራ ክልል የሚገኙት ተፈናቃዮች፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በክልላዊ ደረጃ በሚደረገው ስብሰባ እና በብሔራዊ ምልዓተ ጉባኤ ላይ፣ ተወካዮቻቸው እንዲሳተፉና መሠረታዊ ያሏቸውን አጀንዳዎች ለማቅረብ እንዲጋበዙ ጠይቀዋል፡፡

በኹሉም ክልሎች ያሉ ተፈናቃዮች፣ በሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፉ እየተደረገ እንደኾነ የተናገሩት የኮሚሽኑ አባል ዶር. ዮናስ አዳዬ፣ በዐማራ እና በትግራይ ክልሎች ያለው የጸጥታ ኹኔታ፣ ተሳታፊዎችንና ቁልፍ ሀገር አቀፍ አጀንዳዎችን የሚለዩበትን የመጀመሪያ ምክክር እንዳያደርጉ ዕንቅፋት እንደፈጠረባቸው አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች፣ ከ4ነጥብ3 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃይ እንደሚገኝ፣ ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM) በቅርቡ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG