ከፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት በኋላ፣ የትግራይ ተፈናቃዮች፣ “በብዛት ወደ ቀዬአቸው ተመልሰዋል፤” በሚል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያወጣው ሪፖርት፣ “ከእውነት የራቀ እና ሓላፊነት የጎደለው” እንደኾነ ጠቅሶ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቃወመ፡፡
የፌዴራሉ መንግሥት፣ በመዋቅሩ በሚወጡ መሰል ጎጂ ሪፖርቶች ላይ፣ የእርምት ርምጃ እንዲወሰድም፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፣ በተፈናቃዮች ጉዳይ የወጣው ሪፖርት፣ የትግራይ ክልልን እንደማያካትት አስታውቆ፣ በሪፖርቱ፣ “ሰሜን ኢትዮጵያ” ተብሎ የተጠቀሰው፣ የዐማራ እና የአፋር ክልሎችን ተፈናቃዮች የሚመለከት እንደኾነ አስረድቷል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡
መድረክ / ፎረም