በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን ጦርነቱ እያየለ ሲሄድ ለጋሽ ሀገራት እየተዳከሙ ነው አለች


የአለም ባንክ እና የአይ ኤም ኤፍ ስብሰባ በማራካሽ ጥቅምት 2016
የአለም ባንክ እና የአይ ኤም ኤፍ ስብሰባ በማራካሽ ጥቅምት 2016

ዩክሬን ለጋሽ ሀገራቶቿ ከፊታቸው በተደቀነው ምርጫ እና በአካባቢያቸው ባለው የጂኦ ፖለቲካል ውጥረት የተነሳ የገንዘብ ድጋፍን ማረጋገጥ እየከበዳት መጥቷል ሲሉ የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር ሴርሂይ ማቼንኮ ትላንት ቅዳሜ አስታወቁ።

ሚኒስትሩ“እጅግ ብዙ መዳከም ይታየኛል። በወዳጆቻችን መካከል ድካም አለ። ጦርነቱን መርሳት ቢሹም ነገር ግን ጦርነቱ በሙሉ ጉልበት እየተካሄደ ነው” በማለት የአለም ባንክ እና አለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ አይ ኤም ኤፍ በማራካሽ ባደጉት ስብሰባ ላይ በትላንትናው ዕለት አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ዩክሬን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር ደጋፊዎችን ለማሳመን ሁለት ዕጥፍ በመስራት ተጠብቆባታል ሲሉ ተናገረዋል። አክለውም ከአለም የገንዘብ ፈንድ የ5.4 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ቃል ተገብቶልናል ይሁን እንጂ ከጃፓን፣ ከዩናይትድ ኪንግደም እና በእርግጠኝነት ቁልፍ አጋራችን ከሆኑት ዩናይትድ ስቴትስ እንዲሁም ከአውሮፓ ህብረት ቃልኪዳን እንጠብቃለን ሲሉ ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የ52.6 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ከመጪው የጎርጎሮሳዊያኑ 2024 እስከ 2027 ባሉት ጊዜያት ለመለገስ እየሰራ የገኛል። ይሁን እንጂ ሚኒስሩ ዩክሬን በመጭው አንድ ዓመት 18 ቢልየን ዶላር እንዲሰጣት እንደምትጠብቅ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል መርቸንኮ በአውሮፓ ህብረት በኩል የሩሲያ መንግስት ንብረቶችን ለማገድ የተጀመረውን ጥረት አድንቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG