በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን ኃይሎች ይዞታቸውን እያጠናከሩ ነው - የኔቶ ዋና ጸሀፊ


በስተግራ የሚታዩት የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጄንስ ስቶተልንበርግ፣ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዜለንስኪ ጋር በኪቭ ካደረጉት ስብሰባ ቀደም ብሎ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ። መስከረም 28፣ 2023.
በስተግራ የሚታዩት የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጄንስ ስቶተልንበርግ፣ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዜለንስኪ ጋር በኪቭ ካደረጉት ስብሰባ ቀደም ብሎ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ። መስከረም 28፣ 2023.

የዩክሬን ኃይሎች በተፋፋመው ከባድ ውጊያው ውስጥ ቀስ በቀስ ይዞታቸውን እያጠናከሩ በመሆኑ አጋሮች ለዩክሬን ተጨማሪ እርዳታ እንዲያደርጉ እና የሚላከውን የመከላከያ መሣሪያዎች ምርት እና አቅርቦት እንዲያፋጥኑ በየጊዜው እያሳሰቡ መሆኑን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት-ኔቶ ዋና ጸሀፊ ጄንስ ስቶተልንበርግ ዛሬ ሐሙስ ተናገሩ፡፡

ስቶልተንበርግ በኪቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ዩክሬን ይበልጥ እየጠነከረች በሄደች ቁጥር የሩሲያን ጥቃት ለማስቆም እየተቃረብን እንመጣለን።” ብለዋል፡፡

ስቶልተንበርግ ከፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ጎን ለጎን ቆመው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኔቶ ለዩክሬን ቁልፍ ተተኳሽ የጦር መሣሪዎች የተመደበ የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ማዕቀፍ ውል አለው ብለዋል።

ዋና ጸሀፊው አያይዘውም “ዩክሬን ጦርነቱን ለማሸነፍ የሚያስፈልጋትን ነገር መስጠት ለኔቶ የደህንነት ጥቅም ነው” በማለት ተናግረዋል፡፡

የዩክሬን ጦር ዛሬ ሀሙስ በሰጠው መግለጫ የአየር መከላከያው ሩሲያ ዩክሬንን ለማጥቃት ሌሊቱን ከላከቻቸው 44 ድርኖች መካከል 34ቱን መቶ ማውረዱን አስታውቋል፡፡

ሩሲያ የጥቃት ኢላማ ያደረገቻቸው አካባቢያዎች ማይኮሌቭ፣ አዴሳ እና ኪሮቮራድ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ ትናንት ረቡዕ ባሰሙት ዕለታዊ የምሽቱ መልዕክታቸው፣ የአገራቸው ተዋጊዎች “የሩሲያን ሚሳዬሎች፣ መድፎችና ሌሎች ተዋጊ ድሮኖችንና የሩሲያን ጦር አውሮፕላኖች ለማውደም ተጨማሪ ነገሮች እንደሚያስፈልጓቸው ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG