እስራኤል፣ በጋዛ ሰርጥ ላይ የምታካሒደውን ድብደባ አጠናክራ ቀጥላለች። በሰርጡ አካባቢ የሚኖሩ ቤተሰቦች ለቀው እንዲወጡ ቢደረግም፣ በሐማስ ታግተው የተወሰዱት ቢያንስ 150 የሚደርሱ እስራኤላውያን ቤተሰቦች ስጋት፣ ከዕለት ወደ ዕለት እያየለ መጥቷል። ጋዛ ውስጥ ሙሉ ከበባ የተደረገባቸው ከሁለት ሚሊዮን በላይ ፍልስጥኤማውያንም፣ ቀንና ሌሊት የከባድ መሣሪያ እየወረደባቸው መፈናፈኛ አጥተዋል።
በዚኽ ኹኔታ ላይ የአሜሪካ ድምፅ ያጠናቀረው ዘገባ ነው፡፡
መድረክ / ፎረም