እስራኤል፣ በጋዛ ሰርጥ ላይ የምታካሒደውን ድብደባ አጠናክራ ቀጥላለች። በሰርጡ አካባቢ የሚኖሩ ቤተሰቦች ለቀው እንዲወጡ ቢደረግም፣ በሐማስ ታግተው የተወሰዱት ቢያንስ 150 የሚደርሱ እስራኤላውያን ቤተሰቦች ስጋት፣ ከዕለት ወደ ዕለት እያየለ መጥቷል። ጋዛ ውስጥ ሙሉ ከበባ የተደረገባቸው ከሁለት ሚሊዮን በላይ ፍልስጥኤማውያንም፣ ቀንና ሌሊት የከባድ መሣሪያ እየወረደባቸው መፈናፈኛ አጥተዋል። በዚኽ ኹኔታ ላይ የአሜሪካ ድምፅ ያጠናቀረው ዘገባ ነው፡፡
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ማርች 14, 2025በአፍሪካ የኅይል አቅርቦት ላይ ያተኮረውና በዋሽንግተን ዲሲ የተካሔደው ጉባኤ
-
ማርች 14, 2025የኢትዮጵያውያት ሴቶች ጥያቄ ምንድን ነው? - የአድማጭ ተመልካቾች አስተያየት
-
ማርች 13, 2025አርቲስት አንዱዓለም ጎሣ ተጨማሪ 13 ቀናትን በእስር እንዲቆይ ፍርድ ቤት ፈቀደ
-
ማርች 13, 2025ሩሲያ የተቆጣጠረቻቸውን የዩክሬን ግዛቶች እንደያዘች መቀጠል ትሻለች