በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእሥራኤል -ጋዛ ጦርነት የኢትዮጵያውያንና ቤተ እስራኤላውያን ጉዳት ገና እንዳልታወቀ ተገለጸ


በእሥራኤል -ጋዛ ጦርነት የኢትዮጵያውያንና ቤተ እስራኤላውያን ጉዳት ገና እንዳልታወቀ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:57 0:00

በእስራኤል ጋዛ ግጭት በኢትዮጵያውያንና ቤተ እስራኤላውያን ላይ ስለደረሰው ጉዳት፣ እስከ አሁን ምንም የታወቀ ነገር እንደሌለ፣ በእስራኤል የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ተስፋየ ይታይህ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

የሮኬት ጥቃቱ ዛሬም ቀጥሏል፤ ያሉት አምባሳደሩ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤላውያን፣ ጥቃቱ በደረሰበት አካባቢ በብዛት እንደሚኖሩ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋራ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላት የጠቀሱት አምባሳደሩ፣ ለየትኛውም አካል ሳትወግን፣ ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ፍላጎቷ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

አምባሳደር ተስፋዬ የሰጡንን አስተያየት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG