በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ ክልል ጎርፍ አሁንም ሰዎችን እያፈናቀለ እንደኾነ ተገለጸ


በጋምቤላ ክልል ጎርፍ አሁንም ሰዎችን እያፈናቀለ እንደኾነ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:12 0:00

በጋምቤላ ክልል ጎርፍ አሁንም ሰዎችን እያፈናቀለ እንደኾነ ተገለጸ

በጋምቤላ ክልል በጂካዎ እና በላሬ ወረዳዎች፣ ትላንት ረቡዕ በደረሰ የጎርፍ አደጋ፣ ከአምስት ሺሕ በላይ ነዋሪዎች ከቀዬአቸው እንደተፈናቀሉ፣ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

በክልሉ፣ በጎርፍ ሳቢያ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች አጠቃላይ ብዛት ከ30ሺሕ በላይ እንደደረሰ፣ የፕሬዚዳንቱ ተወካይ እና የጸጥታ እና የሰላም ግንባታ ቢሮ ምክትል ሓላፊ አቶ ዑሞድ ዑሞድ ጠቁመዋል፡፡ በትምህርት ቤት፣ በቤተ ክርስቲያንና በመስጊድ ውስጥ የተጠለሉ ተፈናቃዮቹ ድጋፍ እንዲያገኙ፣ መንግሥት ከግብረ ሠናይ ድርጅቶች ጋራ እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ጎርፉ ያስከተለው ቁሳዊ ውድመት እየተለየ ነው ያሉት አቶ ዑሞድ፣ በመጠለያነት እያገለገሉ ያሉት ትምህርት ቤቶች ባለመለቀቃቸው፣ የዓመቱ የመማር ማስተማር ሒደት እስከ አሁን እንዳልተጀመረ፣ አክለው ተናግረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ)

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG