በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥት የሦስት ዓመት ኢኮኖሚያዊ እድገት ስኬት ከእውነታው ጋራ እንደማይጣጣም ባለሞያዎች ተቹ


የመንግሥት የሦስት ዓመት ኢኮኖሚያዊ እድገት ስኬት ከእውነታው ጋራ እንደማይጣጣም ባለሞያዎች ተቹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:09 0:00

የመንግሥት የሦስት ዓመት ኢኮኖሚያዊ እድገት ስኬት ከእውነታው ጋራ እንደማይጣጣም ባለሞያዎች ተቹ

ኢትዮጵያ፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት፣ የኮቪድ-19ኝን ወረርሽኝ ጨምሮ፣ በልዩ ልዩ ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ብታልፍም፣ የ6ነጥብ3 በመቶ አማካይ ኢኮኖሚያዊ እድገት ማስመዝገብ እንደቻለች፣ መንግሥት አስታወቋል፡፡

ይህ የተገለጸው፣ ከ2013 እስከ 2015 ዓ.ም. ያለውን የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ የሦስት ዓመታት አፈጻጸም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከካቢኔአቸው ጋራ ኾነው፣ ባለፈው ሳምንት በገመገሙበት ወቅት ነው፡፡

በዐዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር አጥላው ዓለሙ፣ ሪፖርቱ፣ አገሪቱ ከነበረችበትና አሁን በመሬት ላይ ካለው እውነታ ጋራ አይጣጣምም፤ ሲሉ ተችተዋል፡፡


የዕቅድ ዝግጅቱ፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት ያጋጠሙ ዓለም አቀፋዊ ኹኔታዎችን ታሳቢ እንዳላደረገ የገለጹት፣ የፋይናንስ እና ምጣኔ ሀብት ባለሞያው አቶ ሚካኤል ዐዲስ በበኩላቸው፥ “ኢኮኖሚው፣ በሪፖርቱ በቀረበው ደረጃ፣ ግቡን አሳክቷል ብሎ ለመቀበል ያስቸግራል፤” ይላሉ፡፡

አስማማዉ አየነው በጉዳዩ ላይ ባለሞያዎችን አነጋግሮ ለዛሬ ንግድ እና ምጣኔ ሀብት ክፍለ ጊዜ ተከታዩን ጥንቅር አዘጋጀቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG