በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡዳፔስቱ ሞቃታማ የአየር ጠባይ እጅግ ፈታኝ እንደነበር ባለወርቅ ሜዳልያ አትሌቶች ገለጹ


የቡዳፔስቱ ሞቃታማ የአየር ጠባይ እጅግ ፈታኝ እንደነበር ባለወርቅ ሜዳልያ አትሌቶች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:43 0:00

የቡዳፔስቱ ሞቃታማ የአየር ጠባይ እጅግ ፈታኝ እንደነበር ባለወርቅ ሜዳልያ አትሌቶች ገለጹ

እጅግ ፈታኙ የቡዳፔስት ሞቃታማ የአየር ጠባይ፣ ለቀጣይ ውድድሮች ዝግጅት መልካም ተሞክሮ እንደሰጣቸው፣ ባለወርቅ ሜዳሊያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተናገሩ፡፡

በሻምፒዮናው ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን፣ ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት፣ ዐዲስ አበባ ሲገባ፣ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

በዓለም አትሌቲክስ ውድድሩ፣ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያዎች ያሸነፉት አትሌቶች ጉዳፍ ጸጋይ እና አማኔ በሪሶ፣ ውድድሩ፥ “በፈታኝ የአየር ኹኔታ ውስጥ ቢደረግም፣ ጥሩ ውጤት ተመዝግቧል፤” ብለዋል፡፡

ቀጣይ የአትሌቶች ዝግጅትም፥ የውድድር ስፍራን የአየር ጠባይ ያገናዘበ መኾን እንደሚኖርበት አመልክተዋል፡፡

በአቀባበል ሥነ ሥርዐቱ ላይ አግኝተን ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎችም፣ ከነበረው ሞቃታማ የአየር ጠባይ አንጻር፣ የተገኘው ውጤት ቢያስደስትም፣ ለወደፊቱ፣ አትሌቶች ጠንካራ ሥራ እንደሚጠበቅባቸው ከውድድሩ እንደተረዱ አስገንዝበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG