በዓለም አትሌቲክስ ውድድሩ፣ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያዎች ያሸነፉት አትሌቶች ጉዳፍ ጸጋይ እና አማኔ በሪሶ፣ ውድድሩ፥ “በፈታኝ የአየር ኹኔታ ውስጥ ቢደረግም፣ ጥሩ ውጤት ተመዝግቧል፤” ብለዋል፡፡
ቀጣይ የአትሌቶች ዝግጅትም፥ የውድድር ስፍራን የአየር ጠባይ ያገናዘበ መኾን እንደሚኖርበት አመልክተዋል፡፡
በአቀባበል ሥነ ሥርዐቱ ላይ አግኝተን ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎችም፣ ከነበረው ሞቃታማ የአየር ጠባይ አንጻር፣ የተገኘው ውጤት ቢያስደስትም፣ ለወደፊቱ፣ አትሌቶች ጠንካራ ሥራ እንደሚጠበቅባቸው ከውድድሩ እንደተረዱ አስገንዝበዋል፡፡