በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ልዩነትን በውይይት የመፍታት ማኅበረሰባዊ ባህል መዳከሙን ባለሞያዎች ተናገሩ


በኢትዮጵያ ልዩነትን በውይይት የመፍታት ማኅበረሰባዊ ባህል መዳከሙን ባለሞያዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:21 0:00

በኢትዮጵያ ልዩነትን በውይይት የመፍታት ማኅበረሰባዊ ባህል መዳከሙን ባለሞያዎች ተናገሩ

ኢትዮጵያ የነበሯት የግጭት መፍቻ ዕሤቶች፣ ከዘመናዊነት ጋራ በአግባቡ እየተጣጣሙ መጠበቅ ባለመቻላቸው፣ አሁን ላይ፣ ልዩነቶችን በውይይት የመፍታት ባህል እየተዳከመ እንደ መጣ፣ ምሁራን ተናገሩ።


የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው ሁለት ምሁራን፣ ማኅበረሰባዊ የችግር መፍቻ ባህሎችን ቅቡልነት ለመመለስ፣ ቀጣይ እና የተቀናጀ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ መክረዋል። ምሁራኑ ሥር እየሰደደ እንደመጣ የገለጹት፣ ልዩነቶችን ከውይይት ይልቅ ኀይልን በማስቀደም የመፍታት ዝንባሌ፣ ከፖለቲከኞች የመነጨ ችግር ነው።
በመኾኑም፣ በማኅበረሰቡ በጎ ዕሤቶች፣ ፖለቲካዊ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት፣ የተሻለች ሀገርን ለትውልድ ለማስረከብ መሥራት እንደሚገባ ምሁራኑ አሳስበዋል።


በጉዳዩ ላይ፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ባህል አካዳሚ መምህሩንና ተመራማሪውን ዶክተር ባይለየኝ ጣሰውንና የታሪክ ተመራማሪውን ዶክተር አየለ በክሪን ያናገረው አስማማው አየነው፣ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጀቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG