በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከቡዳፔስቱ የአምስት ሺሕ ሜትር ውድድር ተሳትፎ ቀሪ የተደረገው አትሌት ቅሬታ እና የፌዴሬሽኑ መግለጫ

ከቡዳፔስቱ የአምስት ሺሕ ሜትር ውድድር ተሳትፎ ቀሪ የተደረገው አትሌት ቅሬታ እና የፌዴሬሽኑ መግለጫ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:52 0:00

ከቡዳፔስቱ የአምስት ሺሕ ሜትር ውድድር ተሳትፎ ቀሪ የተደረገው አትሌት ቅሬታ እና የፌዴሬሽኑ መግለጫ

በሀንጋሪ ቡዳፔስት የአትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደረው ቡድን አባል የኾነው አትሌት ጥላሁን ኀይሌ፣ በአምስት ሺሕ ሜትር ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶችን አስመልክቶ የተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም፣ በማኅበራዊ የመገናኛ ትስስሮች ቅሬታውን አሰምቷል።

በውድድሩ ለመሳተፍ የሚያበቃውን ሰዓት እና የአካል ብቃት አሟልቶ ወደ ውድድሩ ስፍራ ከመጣ በኋላ፣ በእርሱ ምትክ አትሌት በሪሁ አረጋዊ እንደሚሳተፍ በመጨረሻ ሰዓት መስማቱ፣ የፈጠረበትን ስሜት አጋርቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ልዑክ፣ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ፣ የአምስት ሺሕ ሜትር የአትሌቶች አሰላላፍ ለውጥ፣ ኢትዮጵያን ውጤታማ ለማድረግ ታልሞ እንደተደረገ አስታውቋል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG