ብሪክስ በሚል የእንግሊዘኛ ምኅጻር የሚታወቀው የአምስት አገሮች ስብስብ፣ ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ፣ ዛሬ፣ በአፍሪካዊቱ የማኅበሩ አባል - በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ከተማ ተጀምሯል። ጉባኤው እስከ ኀሙስ ይዘልቃል፡፡ ተጨማሪ አባል ሀገራትን ተቀብሎ ተቋሙን የማስፋፋት ጉዳይ፣ መሪዎቹ የሚወያዩበት ግንባር ቀደም አጀንዳ እንደሚኾን ይጠበቃል።
አምስቱ የብሪክስ አባል ሀገራት፡- ሩስያ፥ ቻይና፥ ሕንድ፥ ብራዚል እና አስተናጋጇ ደቡብ አፍሪካ ናቸው። ቻይና፣ ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ፥ ብሪክስ፣ ዐዲስ አባላትን እየተቀበለ እንዲስፋፋ አጥብቀው ይደግፋሉ።
ይህ በዚኽ እንዳለ፣ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ ከብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፣ በሀገራቸው ይፋዊ ጉብኝት ለሚያደርጉት ለቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ የሞቀ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የኬት ባርትሌት እና ዴረን ቴይለርን ዘገባዎች ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።