በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒዤር ሁንታው ዐዲስ መንግሥት መሠረተ


የኒጀር ወታደራዊ መሪዎች ሐምሌ 2015
የኒጀር ወታደራዊ መሪዎች ሐምሌ 2015
በኒዤር ሥልጣን የነጠቀው ሁንታ፣ ዐዲስ መንግሥት ማቋቋሙን፣ በብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያው በተነበበ ዐዋጅ አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው በሁንታው የተሠየሙት፣ ዓሊ ማሐማን ላሚን ዘይን ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ 21 አባላት ያሉትን ካቢኔ እንደሚመሩ፣ በዐዋጁ ተመልክቷል።
በዐዲሱ ወታደራዊ አገዛዝ ም/ቤት ውስጥ ያሉ ጄነራሎች፣ መከላከያውንና የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ይመራሉ፤ ተብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ(ኤኮዋስ) አባል አገራት፣ በኒዤር ጉዳይ፣ በናይጄሪያ መዲና ዝግ ስብሰባ በማድረግ ላይ ናቸው።
ሁንታው ሥልጣኑን መልሶ ለፕሬዚዳንት ሞሐመድ ባዙም እንዲያስረክብ፣ እስካለፈው እሑድ ድረስ ቀነ ገደብ ሲያስቀምጥ፣ ካልኾነ ግን፣ በወታደራዊ መንገድ ጣልቃ እንደሚገባ አስታውቆ ነበር። ሁንታው በበኩሉ፣ ማንኛውንም የውይይት ሐሳብ ሳይቀበል ቀርቷል።
በሌላ በኩል፣ ከሁለት ሳምንታት በፊት፣ ከሥልጣን የተወገዱትና በቤት ውስጥ እስር ላይ ያሉት፣ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ባዙም፣ “ቀለባቸው እያለቀ ነው፤” ሲል አሶሺዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG