በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት በስልክ እንደተወያዩ ገለጹ


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት በስልክ እንደተወያዩ ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:32 0:00

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት በስልክ እንደተወያዩ ገለጹ

ሩሲያ፣ በዩክሬን የእህል ምርት ኤክስፖርት ላይ እየፈጠረች ያለው ተጽእኖ አስመልክቶ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋራ እንደተወያዩ፣ ፕሬዚዳንት ዜሌኒስኪ አስታውቀዋል፡፡

ዩክሬን፣ ለዓለም የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ያላትን የመሪነት ሚና ለመቀጠል ዝግጁ እንደኾነች የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ኾኖም ሩሲያ፣ የዩክሬንን የባሕር ላይ እንቅስቃሴን መገደቧ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለዓለም በሚቀርበው የእህል አቅርቦት ላይ ተጽእኖ እየፈጠረ እንደኾነ አብራርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው፣ “ከፕሬዚዳንት ዘሌንስኪ ጋራ፣ በሁለትዮሽ እና በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች” ላይ መወያየታቸውን ከመጥቀስ ባለፈ፣ ዝርዝር ጉዳዮችን አልጠቀሱም፡፡

በጥቁር ባሕር በኩል፣ ዩክሬን የእህል እና የማዳበሪያ ምርቶቿን ወደ ወጪ ገበያ እንድትልክ የተደረሰው ስምምነት፣ ከአንድ ዓመት ያህል ቆይታ በኋላ፣ ሩሲያ ልታስቀጥለው ባለመስማማቷ፣ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እንዲታቀብ ማድረጓ ይታወቃል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ሁለት የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች፣ አቶ ክቡር ገና እና ፕር. ዓለማየሁ ገዳ፣ የተለያዩ ሐሳቦችን አንጸባርቀዋል፡፡

የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤቶች ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክቡር ገና፣ የስምምነቱ መቋረጥ ተጽእኖ፣ እንደ ኢትዮጵያ ካሉ አዳጊ ሀገራት ይልቅ፣ የዩክሬን የእህል ምርቶችን በብዛት ወደ አገራቸው በሚያስገቡ ሀገራት ላይ ከብዶ ይታያል፤ ሲሉ፣ ፕር. ዓለማየሁ በበኩላቸው፣ አዳጊ ሀገራትም፣ በቀጥታ ይኹን በተዘዋዋሪ ጉልሕ ተጎጂዎች ናቸው፤ ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG