በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ሰልፍ የወጡ ሴቶች ሰብአዊ ርዳታው እንዲቀጠልና የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዲተገበር ጠየቁ


በትግራይ ሰልፍ የወጡ ሴቶች ሰብአዊ ርዳታው እንዲቀጠልና የፕሪቶሪያው ስምምነት እንዲተገበር ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:15 0:00

በትግራይ ሰልፍ የወጡ ሴቶች ሰብአዊ ርዳታው እንዲቀጠልና የፕሪቶሪያው ስምምነት በምልአት እንዲተገበር ጠየቁ

በትግራይ ክልል ልዩ ልዩ ከተሞች ሰልፉ ያካሔዱ ሴቶች፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው ይመለሱ፤ የተቋረጠው ሰብአዊ ድጋፍ ይቀጥል፤ በጦርነቱ ወቅት በደል የፈጸሙ ለሕግ ይቅረቡ፤ የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። የትግራይ ሴቶች ማኅበር በአዘጋጀው በዚኹ ሰልፍ፣ የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ተሳታፊዎቹ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

መቐለን ጨምሮ በትግራይ ክልል ከተሞች፣ ትላንት እሑድ፣ ሐምሌ 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ሰልፍ የወጡ ከሁለት ሺሕ በላይ ሴቶች፣ የፕሪቶሪያው ዘለቄታዊ የተኩስ አቁም የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ጠይቀዋል።

ሰልፉ በተመሳሳይ፣ በሽረ እንዳሥላሴ፣ በአኵስም እና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች እንደተካሔደ፣ የትግራይ ሴቶች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ አበባ ኃይለ ሥላሴ ተናግረዋል።

ከመቐለው ሰልፍ ተሳታፊዎች አንዷ ወይዘሮ ርግበ ኣብርሃ፣ ሰብአዊ ድጋፉ በመቋረጡ በተለይ ሴቶች እና ሕፃናት እየተጎዱ እንደኾኑና ርዳታው እንዲቀጥል ለመጠየቅ እና በጦርነቱ ወቅት በሰላማዊ ዜጎች በተለይ በሴቶች ላይ በደል የፈጸሙ አካላትም ተጠያቂ እንዲኾኑ ድምፃቸውን እንዳሰሙ ገልጸዋል።

ሌላዋ የሰልፉ ተሳታፊ ወይዘሮ ቅብእቱ ሓጎስ በበኩላቸው፣ በጦርነቱ ምክንያት፣ ከጸገዴ ወረዳ ተፈናቅለው በመጠለያ ማእከል ውስጥ በችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረው፣ ይህንም ዓለም አቀፍ ማኅብረሰብ እንዲገነዘብላቸው አመልክተዋል፡፡

የትግራይ ሴቶች ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ አበባ ኃይለ ሥላሴ፣ የሰላም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ባለመተግበሩ፣ በተለይ ሴቶች ችግር ውስጥ ይገኛሉ፤ ብለዋል፡፡

በሰልፉ ሴቶች ስላነሧቸው ጉዳዮች የጠየቅናቸው፣ የትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም፣ ጥያቄዎቹ ተገቢ እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርም ምላሽ እንዲሰጥባቸው ከፌዴራሉ መንግሥት ጋራ እየተወያየበት እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

በተያያዘ ከጦርነቱ በፊት ትግራይ ክልል ይሠሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት፤ "ጦርነቱ ላይ አልተሳተፋችሁም" በሚል ደሞዝ መከልከላቸውን ገልፀው በዛሬው ዕለት በክልሉ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ቅሬታ አሰምተዋል::

ከክልሉ የተለያዩ ከተሞች ከሚገኙ 1 ሺሕ ከሚኾኑ የፖሊስ አባላት መወከላቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት ከቅሬታ አቅራቢዎቹ አንዱ፤ ረዳት ኢንስፔክተር ጳውሎስ ስብሃቱ ፤ “በጦርነቱ አልተሳተፋችሁም ፤ በ2013 ዓመተ ምህረት ክልሉን ሲያስተዳድር ከነበረው ጊዜያዊ አስተዳደር ደሞዝ ተቀብላችኋል” በሚል ደሞዝ መከልከላቸውን ገልፀዋል። መፍትሄ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱን ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG