የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን፤ የቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ከሩሲያው ፕሬዘዳንት ብላድሚር ፑቲን ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ ‘ተጠንቀቁ’ በማለት ቤጂንግ በአሜሪካ ኢንቨስትመንት ላይ የተደገፈች ሀገር ናት ሲሉ ከሲኤኤን የዜና ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስጠንቅቀዋል።
“ይኸንን የምለው ለማስፈራራት ሳይሆን ይሄ ምልከታ ነው” ሲሉ ፕሬዘዳንቱ ተናግረዋል።
“ሩሲያ ወደ ዩክሬን ከዘለቀች በኋላ 600 የሚሆኑ የአሜሪካ ኩባኒያዎች ሩሲያን ለቀው ወጥተዋል።” ያሉት ፕሬዘዳንቱ “ምጣኔ ሃብታችን በአሜሪካ እና በአውሮፓ ከሚገኙ ኢንቨስትመንቶች ላይ የተመሰረተ ነው ብለውኛል ስለዚህ ይጠንቀቁ !ይጠንቀቁ” ብለዋል።"
ፑቲን እና የቻይናው ፕሬዘዳንት ሺ በመጋቢት ወር ላይ ለሁለት ቀናት የወዳጅነት ንግግር ያደረጉ ሲሆን በጋራ በመሆን ምዕራቡን ዓለም ተችተዋል። ይሁን እንጂ በዩክሬን ጉዳይ ምንም ዓይነት የዲፕሎማሲያዊ ለውጥ አልታየም።
ሁለቱም መሪዎች በዚህ ሳምንት በጋራ የመሪዎች ስብሰባ ላይ በድረገጽ አማካኝነት ተሳትፈዋል። በአሜሪካ እና በቻይና ግንኙነት ዙሪያ፤ የታዋይን ጉዳይ፣ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት እና የዩናይትድ ስቴትስ የኤክስፖርት ገደብ በመሳሰሉት የተነሳ ውጥረቶች ከፍ እያሉ ሄደዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት ሃላፊ ጃኔት ዬለን ከቅዳሜ ዕለት አንስቶ በቻይና ጉብኝታቸውን ቀጥለዋል።
ፕረዘዳንት ሺ በባይደን ንግግር ላይ አስተያየታቸውን ተጠይቀው “ሰምቷል፤ ነገር ግን አልተከራከረም፤ ልብ ስላለም ወደ ሩሲያ ጉዳይ ላይ ጠለቅ ብሎ አልገባም” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “ይሄንን ነገር ልናስተካክለው እንችላለን ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።