በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ቻይናን እየጎበኙ ነው


 የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የለን፣ ቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቺያንግ፤ ቤጂንግ፣ ቻይና
የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የለን፣ ቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቺያንግ፤ ቤጂንግ፣ ቻይና

ቻይናን ለአራት ቀናት ለመጎብኘት ወደዚያው ያቀኑት የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የለን ዛሬ ዓርብ ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቺያንግ ጋር ቤጂንግ ውስጥ ተወያይተዋል፡፡

የለን፣ በሁለቱ አገሮች መካከል የሰፈነውን ውጥረት ለማርገብ፣ ግንኙነታቸውን ማሻሻል እንደሚገባ በጉብኝታቸው የመጀመሪያው ቀን በነበራቸው ውይይት ላይ ተናግረዋል፡፡

“ይህ ጉብኝት በሁለቱ አገሮች መካካከል ይበልጥ ተከታታይ የሆኑ መደበኛ የግንኙነት መስመሮችን እንደሚከፍትም ተስፋዬ ነው፣ በዚያ መንፈስ ተከታዩን ውይይታችንን በጉጉት እጠብቃለሁ” ብለዋል የለን፡፡

የለን ቀደም ሲል ቻይና ውስጥ ከተሰማሩ የአሜሪካ የንግድ ድርጅቶች ጋር ስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡ በዓለም ሁለተኛው ትልቅ ኢኮኖሚ ባላት ቻይና ውስጥ የገበያ ማሻሻያ እንዲደረግ በዚሁ ስብሰባ ጥሪያቸውን ያቀረቡት የለን፣ “ኢፍትሃዊ የኢኮኖሚ አሠራር” ሲሉ የጠሩትን የቻይናን ድርጊት ዩናይትድ ስቴትስና አጋሮችዋ እንደሚታገሉት አስጠንቅቀዋል፡፡

የለን ማስጠንቀቂያውን የሰጡት የፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የቅርብ ታማኝ ባለሟል እና የቀድሞ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ከነበሩት የቻይና ኢኮኖሚ ዋና አማካሪ ሊየው ኽ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG