በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘለንስኪ የሩሲያ ወረራ 500ኛ ቀን በስኔክ አይላንድ ዘከሩ


የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም
የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም

የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረችበት አንስቶ 500 ቀናት መሙላቱን በማስመልከት ዛሬ ቅዳሜ በተዘጋጀ መሰናዶ ላይ ወታደሮቻቸውን አመሰግኑ።

“እያንዳንዱ ወታደር... ታጣቂ ኃይሎቻችን፣ የስለላ፣ ብሔራዊ ጥበቃ፣ የድንበር አስከባሪ፣ ብሄራዊ ፖሊስ፣ የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት፣ ተወካዮቻችን እና እንዲሁም ዜጎቻችን ሆይ አመሰግናለን። ለዩክሬን ስለምትዋጉላት አመሰግናለሁ። በእርግጠኝነት እናሸንፋለን” ብለዋል።

ዘለንስኪ ዕለቱ ስኔክ አይላንድ በመባል በሚታወቅ ስፍራ እንዲታሰብ ላይ ያደረጉ ሲሆን፤ ስፍራው ቀደም ሲል ጥቁር ባህርን ሲጠብቁ የነበሩ የዩክሬን ወታደሮች ለሩሲያ እጅ ስጡ የሚል ጥያቄ ቆምጨጭ ያለ ምላሽ የሰጡበት ነው። ሩሲያ ደሴቱን ይዛ የነበረ ቢሆንም ዩክሬን በድጋሚ ተቆጣጥራዋለች።

XS
SM
MD
LG