በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዋግነሩ መሪ ቤላሩስ እንዲሄዱ ሩሲያ በድርድር ፈቀደች


ይቭጌኔ ፕሪጎዢን 2023
ይቭጌኔ ፕሪጎዢን 2023

ክሬምሊን በሞስኮ አመራሮች ላይ ተዋጊዎቹን የሰበቀው የዋግነር ተዋጊ ቡድን፤ መሪ የሆኑት ይቭጌኒ ፕሪጎዢን ወደ ቤላሩስ እንዲጓዙ እና አመጽን በማቀጣጠል የተነሳባቸው ክስ ውድቅ እንደሚሆን ትላንት ቅዳሜ አስታወቀ።

የቤላሩስ ፕሬዘዳንት አሌግዛንደር ሉክሼኮ ከሩሲያው ፕሬዘዳንት ብልድሚር ፑቲን ባገኙት ይሁንታ መሰረት ከዋግነሩ መሪ ጋር መደራደራቸውን ቢሯቸው አስታውቋል። ሉክሼንኮ ፕሪጎዢን ለ20 ዓመታት ያህል በግል አውቀዋለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

የክሬምሊኑ ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የዋግነር ተዋጊዎች ምንም ዓይነት ቅጣት አይጠብቃቸውም ሲሉ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ አረጋግጠዋል። ፔስኮቭ “ሁሌም ቢሆን የዋግነር ተዋጊዎች ከፊት በመሆን የፈጸሙትን የጀግንነት ተግባር እናከብራለን” ያሉ ሲሆን አያይዘም ሞስኮ የቤላሩስ ፕሬዘዳንት ሉካሼንኮ ግጭቱ እንዳይባባስ ለተጫወቱት ሚና ታመሰግናለች ብለዋል። በአመጹ ላይ ያልተሳተፉት ተዋጊዎችም በቀጣይ አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሁሉንም በጎ ፍቃደኛ አካል በአንድ ላይ ማጠቃለል በሚሻው በመከላከያ ሚኒስቴር ውል በኩል ይቀርብላቸዋል ብለዋል።

ቃል አቀባዩ ፕሬጎዢ ሃይላቸውን እንዲያስወጡ በፕሬዘዳንት ፑቲን ከተሰጠው የደህነት ማረጋገጫ ውጭ የተደረገ ውለታ መኖሩን ይፋ አላደረጉም። ይሁን እንጂ የአርብ ዕለቱን ክስተት “አሳዛኝ” ሲሉ ጠርተውታል።

XS
SM
MD
LG