በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን እና ሞዲ፣ በሰብዓዊ መብትና ዲሞክራሲ ጉዳይ ህንድ የሚቀርብባትን ነቀፌታ አስተባበሉ


የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ

ዩናይትድ ስቴትስ የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር በከፍተኛ ድምቀት ተቀብላ ስታስተናግድ፣ የሰብዓዊ መብት እና የዲሞክራሲያዊ እሴቶች ጉዳይ ወደ ጎን ተትተዋል የሚለውን ነቀፌታ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አስተባብለዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ እና በህንድ መካከል ያለው ግንኙነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ጎልቶ የሚታይና ተጽእኖ ፈጣሪ ግንኙነት እንደሆነ ቀድሞውንም አምን ነበር”

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር በትናንትናው ዕለት ለዩናይትድ ስቴትስ ም/ቤት ንግግር አድርገዋል። በዋይት ሃውስም የክብር የዕራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል።

ፕሬዝደንት ባይደን፣ የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ትናንት በዋይት ሃውስ በተቀበሉበት ወቅት፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የጠነከረ ግንኙነት በተመለከተ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

“በዩናይትድ ስቴትስ እና በህንድ መካከል ያለው ግንኙነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ጎልቶ የሚታይና ተጽእኖ ፈጣሪ ግንኙነት እንደሆነ ቀድሞውንም አምን ነበር” ብለዋል ባይደን።

በዚህ ወቅት፣ የህንድ እና የዩናይትድ ስቴትስ ወዳጅነት መላውን ዓለም ለማጠናከር ጉልህ ሚና አለው”

ሞዲም በዓለም አዲስ የግንኙነት ሥርዓት ቅርጽ በመያዝ ላይ ነው በማለት የፕሬዚደንት ባይደንን መልዕክት አስተጋብተዋል።

“በዚህ ወቅት፣ የህንድ እና የዩናይትድ ስቴትስ ወዳጅነት መላውን ዓለም ለማጠናከር ጉልህ ሚና አለው” ሲሉ ተናግረዋል ሞዲ።

ዩናይትድ ስቴትስ ከሩሲያ ጋር ውዝግብ ውስጥ ባለችበት ሁኔታና፣ ከቻይና ጋርም ያላት ውጥረት እየጨመረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በዓለም በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነችው ህንድ፣ በዋሽንግተን አስተዳደር ሙገሳን እየተቸራት ይገኛል። ተቺዎች እንደሚሉት፣ ዋሽንግተን ይህን በማድረግ ላይ ያለችው፣ የሰብዓዊ መብት ጉዳይን ወደ ጎን ቸል በማለት ነው። ባይደን በዚህ አይስማሙም።

“ዩናይትድ ስቴትስ ከቻይና ጋር ያላት ግንኙነት፣ ከህንድ ጋር እንዳላት ግንኙነት አንድ ዓይነት ያልሆነበት ዋናው ምክንያት፣ በዩናይትድ ስቴትስ እና በህንድ መካከል ከፍተኛ የሆነ መከባበር ስላለ ነው። ምክንያቱም ሁለቱም ዲሞክራሲያዊ አገሮች ናቸውና” ሲሉ ተከላክለዋል ባይደን።

ባይደንና ሞዲ፥ ሕንድ በሰብአዊ መብቶች እና በዴሞክራሲ ጉዳዮች መነቀፏን አስተባበሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:09 0:00

ሞዲም በበኩላቸው፣ መንግስታቸው እዳጣን ማኅበረሰቦች ላይ ጥቃት ያደርሳል፤ እንዲሁም፣ የተቃዋሚዎችን ድምጽ ያፍናል መባሉን አስተባብለዋል።

“ህንድ እና አሜሪካ፤ ሁለቱም አገራት፣ ዲሞክራሲ በዘረ-መላችን ውስጥ ያለ ነገር ነው። ጥልቀት ያለው ዲሞክራሲ መንፈሳችን ነው። ዲሞክራሲ በደም ሥራችን ውስጥ ይዘዋወራል” ብለዋል ሞዲ።

ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላት ግንኙነት በጣም አስፈላጊ ግንኙነት ነው። ግን ደግሞ እኛ ካሉን እሴቶች አንጻር ማየት አለብን። ህንድ የዜጎቿን ሰብዓዊ መብት መጠበቅን በተመለከተ ብዙ መሥራት ይጠበቅባታል”

ባይደን ከህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በሚኖራቸው ቆይታ፣ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን እንዲያነሱ፣ 70 የሚሆኑ የም/ቤት ዓባላት ጠይቀው ነበር።

“ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላት ግንኙነት በጣም አስፈላጊ ግንኙነት ነው። ግን ደግሞ እኛ ካሉን እሴቶች አንጻር ማየት አለብን። ህንድ የዜጎቿን ሰብዓዊ መብት መጠበቅን በተመለከተ ብዙ መሥራት ይጠበቅባታል” ብለዋል ከጠያቂዎቹ አንዱ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ሴናተር ቤን ካርዲን።

ይህም ሆኖ፣ ሞዲ ለሁለቱ የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ ም/ቤቶች የጋራ ጉባኤ ንግግር እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል። ይህም ለውጪ አገር መንግስታት መሪዎች የሚሰጥ ታላቅ ክብር ነው። ሞዲ ለጋራ ም/ቤቱ ሁለት ግዜ ንግግር ያደረጉ የመጀመሪያው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው። ሞዲ በንግግራቸው በሚሊዮን ስለሚቆጠሩት ህንድ አሜሪካውያን ጉዳይ በተለይ አንስተዋል።

“አንዳንዶቹ በዚህ ም/ቤት ውስጥ በኩራት ተቀምጠው ይታያሉ። ከበስተዋላዬ አንዷ ትገኛለች፡፡ ታሪክ ሰርታለች” ብለዋል ሞዲ ወደ ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሃሪስ እያመለከቱ።

ሞዲ በተጨማሪም በመከላከያ እና በአዲስ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው ተናግረዋል።

ትናንት ሃሙስ ማታም፣ በዋይት ሃውስ የክብር ዕራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል።

ሥጋ ለማይበሉቱ የተዘጋጀውን የአትክልት ዕራት ተጋብዘዋል።

XS
SM
MD
LG