በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አሜሪካንን በመጎብኘት ላይ ናቸው


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዋይት ሃውስ ዛሬ ተቀብለው አነጋግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዋይት ሃውስ ዛሬ ተቀብለው አነጋግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዋይት ሃውስ ዛሬ ተቀብለው አነጋግረዋል።

“ዓለም የገጠማት ችግር ህንድ እና አሜሪካ ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚጠይቅ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል ባይደን። “ያንንም በማድረግ ላይ ነን” ሲሉ አክለዋል፡፡

“የሞዲ ጉብኝት ነጻ፣ ግልጽ፣ የበለጸገ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ኢንዶ ፓሲፊክ ቀጠናን የሚፈጠር እና፤ በቴክኖሎጂ፣ መከላከያ፣ ንጹህ ሃይል እንዲሆም በህዋ መስክ የሁለቱን አገራት ትብብር የሚያጠናክር ነው” ብሏል ሁለቱ መሪዎች ከመገናኘታቸው ቀደም ብሎ የወጣው የዋይት ሃውስ መግለጫ።

ዓለም የገጠማት ችግር ህንድ እና አሜሪካ ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚጠይቅ ነው”

ሞዲ በቆይታቸው ለአሜሪካ ኮንግረስ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ለሞዲ ባልተለመደ ሁኔታም፣ ሁለቱ መሪዎች አንድ ላይ በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ህንድ ቁልፍ አጋር መሆናን ለማሳየት፣ ከዚህ በፊት የነበሩት አራት ፕሬዝደንቶች 15 ሰዓታት የሚፈጀውን ጉዞ ወድ ህንድ አድርገዋል።

እንደ ባይደን ግን በዚህ ደረጃ ሞዲን በክብር የተቀበለ ፕሬዝደንት አልነበረም ሲሉ የቪኦኤ የዋይት ሃውስ ዘጋቢዎች በሪፖርታቸው አመልክተዋል። ሙሉ የክብር ዘብ አቀባበል እና ከዋይት ሃውስ ባሻገር በሚገኘውና ብሌየር ሃውስ ተብሎ በሚጠራው የእንግዳ መቀበያ የእራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል።

XS
SM
MD
LG