በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባህር ዳር ገቡ


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባህር ዳር ገቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:33 0:00

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባህር ዳር ገቡ

በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት አመታት የተካሄደው ጦርነት ከጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልዑካን ቡድን፣ ዛሬ ወደ ባህር ዳር ከተማ አምርቶ ከከተማው ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይቷል።

ትራንስፖርትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር እና የህዝብን ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ ቁርጠኛ መሆናቸውንም የአማራ እና የትግራይ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች አስታውቀዋል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራው ልዑክ ዛሬ ረፋዱ ላይ ባህር ዳር ከተማ ሲገባ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገዋል።

ከሀይማኖት አባቶች፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከሴቶችና ከወጣቶች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር አጭር ውይይት ያደረጉት የአማራና የትግራይ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተካሄደውን የሰላም ስምምነት ከፖለቲካ አመራሩ አልፎ ወደ ህዝቡ የማውረድ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ለህዝቦች ሰላም እና አብሮነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች በበርካታ ዘርፎች መከናወን እንዳለበት ጠቁመዋል።

በአማራና በትግራይ ህዝቦች መካከል ጦርነት እንዲካሄድ ያደረጉ አመራሮችን ተጠያቂነት በተመለከተ ከማህበረሰቡ ተከወካዮች ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት አቶ ጌታቸው ረዳ "መጠየቅ ያለበት ሁሉ ይጠየቃል" ብለዋል።

ከሰሜኑ የኢትዮጵያው ጦርነት በኃላ የትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ወደ አማራ ክልል ሲመጡ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።

XS
SM
MD
LG