በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግብር እፎይታ ሊበረታታ የሚገባው የልጆች ትምህርት መርጃዎች አቅርቦት - የ“ፊደል ጥሩ” ተቋም አብነት


በግብር እፎይታ ሊበረታታ የሚገባው የልጆች ትምህርት መርጃዎች አቅርቦት - የ“ፊደል ጥሩ” ተቋም አብነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:48 0:00

በግብር እፎይታ ሊበረታታ የሚገባው የልጆች ትምህርት መርጃዎች አቅርቦት - የ“ፊደል ጥሩ” ተቋም አብነት

“ፊደል ጥሩ” የልጆች ትምህርት መርጃ ተቋም፣ ከአራት ዓመታት በፊት የተመሠረተ ተቋም ነው። ተቋሙ በዋናነት፣ ዕድሜያቸው እስከ ሰባት ዓመት ለኾናቸው ሕፃናት፥ የዐማርኛ ፊደላትን መልክእ ማስለየትን፣ ማንበብ እና መጻፍ ማስቻልን ዓላማው አድርጎ ይሠራል። ከመጻሕፍት በተጨማሪ፣ የተለያዩ ፊደላትን የያዙ ካርዶች፣ እንዲሁም ከዕንጨት እና ከፕላስቲክ የተሠሩ የልጆች ትምህርት መርጃዎችንም ያመርታል።

ከእነዚኽም ባሻገር፣ የኦቲዝም የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውንና መስማት የተሳናቸውን ሕፃናትን የሚያግዙ መርጃዎችንም እንደሚያዘጋጅ፣ የተቋሙ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ራሔል ጸጋዬ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጻለች። በተለይም በሀገሪቱ፣ ከቅድመ ሙዓለ ሕፃናት እስከ አምስተኛ ክፍል ያሉ ልጆች፥ የፊደል መልክእ የመለየት፣ የንባብ እና የመጻፍ ክሂል መሻሻል የሚችለው፣ በትምህርት አቅርቦት እና ጥራት ላይ አተኩሮ በመሥራት እንደኾነ ታሳስባለች።

“ፊደል ጥሩ”ም ኾነ ሌሎች የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን የሚያመርቱ ተቋማት፣ ስኬታማ እንዲኾኑና የትምህርት ሥርዐቱን መደግፍ እንዲችሉ፣ መንግሥት፥ ከመጻሕፍት ውጭ ባሉ መርጃዎች ላይ የሚተምነውን ግብር ሊያቆም ይገባል፤ ትላለች። ይልቁንም እነዚኽን ተቋማት፣ የመንግሥት ጨረታዎች ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ፣ የሕፃናት የትምህርት አቀባበልን ማሳደግ፣ እንዲሁም ደግሞ ሰፊ የሥራ ዕድልን መፍጠር እንደሚቻል ጠቁማለች።

በተጨማሪም፣ ምግባረ ሠናይ ተቋማት፣ ምርቶቹን ገዝተው ለችግረኛ ቤተሰቦች፣ እንዲሁም ለትምህርት ቤቶች ቢለግሱ መልካም እንደሚኾን ታመለክታለች። በአሁን ሰዓት ተቋሙ፣ በዐዲስ አበባ ልዩ ልዩ ቦታዎች፣ የሽያጭ ሱቆች ያሉት ሲኾን፣ ከዐማርኛ የትምህርት መርጃዎች ጋራ፣ የትግርኛ እና የአፋን ኦሮሞ መርጃዎችንም ያቀርባል፤ ስትል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግራለች።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG